ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ በኢትዮጵያ በቅርቡ በተጀመረው የካፒታል ገበያ የመጀመሪያው የግል የኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
የኢንቨስትመንት ባንኩ ይህን ያስታወቀው ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በተካሄደ መርሃ-ግብር ላይ ነው፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤልን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የኢንቨስትመንት ባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አክሊሉ ውበት ባደረጉት ንግግር፣ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ በ385 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው አክለውም የኢንቨስትመንት ባንኩ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለፈው መጋቢት ወር የስራ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውሰዋል። እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ፣ ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም የንግድ አባልነት ምዝገባ በማከናወን ካፒታል ገበያውን በቀዳሚነት ተቀላቅሏል ብለዋል።
ኢንቨስትመንት ባንኩ በአደረጃጀት፤ በማኔጅመንት እና በምከተለው የአስራር ስርዓት ከወጋገን ባንክ አ.ማ ሙሉ በሙሉ የተለየሁ መሆኔን እወቁልኝ ብሏል።
