በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ያስተዋወቁት ጀግኖች ገቡ

Date:

ታምራት እና ቶማስ TT Boys የሚባል የሰርከስ ቡድን መስርተው በመላው አለም በተለይም በሰሜን አሜሪካ ላለፉት ሁለት አሰርት በጥበብ ያሉ ወጣቶች ናቸው።

ሁለት አሰርት በጥበብ የቆዩት የሶስት አመት ልጆች ሳሉ የጀመሩት ጥበብ በመሆኑ ነው። ከለጋነታቸው ጀምሮ በሰርከስ ጥበብ አለምን ዞረው ከየት መጣችሁ ሲባሉ ከታላቋ ኢትዮጵያ እያሉ በመደነቅ ኖረዋል።

በተለይ በሎስ አንጀለስ በታላላቅ መድረኮች እና መገናኛ ብዙሃን ቀርበው ስለኢትዮጵያ ሀገራቸው ተናግረዋል። በተለይም የአለም ድንቅ የእግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲን ጥበብ የሚገልፀው Messi 10 ፊልም ላይ ከራሱ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ሰርተዋል። አድናቆትም ተቸረዋል።

አሁን ደግሞ በቅርቡ በታላቁ የAmerica Got Talent መድረክ ጥበባቸውን አቅርበዉ፣ እጅግ ተደንቀው የሀገራቸውን ስም በበጎ አስነስተዋል፣ በአራቱም ዳኞች ውጤት ወደሚቀጥለው ዙር አልፈው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ዛሬ እንኳን በስኬት ወደሀገራችሁ ተመለሳችሁ፣ አሁንስ ምን እናግዝ ብለን ከጀግኖቹ ጋር ቆይተናል። በሚቀጥለው ዙር ፉክክር ስለሚረዷቸው ጉዳዮች ተመካክረናል። በአጠቃላይም ስለሀገራችን የሰርከስ ጥበብ ጉዳይ ተወያይተናል።

በሚቀጥለው ዙር ውድድር ጀግኖቹ ይበልጥ ደምቀው እንዲያደምቁን፣ የሀገራቸውንም ስም እንዲያደምቁ ልናግዛቸው ይገባል።


ከነብዩ ባዬ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...