በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

Date:

በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቀርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ።

የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ሰራዊት ዲባባ እንደገለጹት ዩኔስኮ 12 የኮንሶ አምባ መንደሮችንና የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤን ዓለም አቀፍ ቅርስ አድርጎ መዝግቧል::

በእነዚህ አምባ መንደሮች ባህላዊ ቤቶች ባህላዊ መሰብሰቢያ ስፍራዎች የትውልድ መቁጠሪያ ትክል እንጨቶች የጀግንነት መዘከሪያ ሀውልቶች እንዲሁም ሌሎች የኮንሶን ህዝብ እሴትን የሚያሳዩ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ቅርሶች እየተጠበቁ ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በአምባ መንደሮቹ ጎጆ ቤቶችን ቆርቆሮ በማልበስ ቅርስነቱን እንዲለቅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቅርሱ ይዘት ላይ የተጋረጠው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው በአሁኑ ሰአትም ከመንደሮቹ ካሉት ቤቶች 50 በመቶ የሚሆኑት ቅርስነታቸውን በሚለቅ መልኩ ቆርቆሮ መልበሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ምክንያቱ ስለ ቅርሱ ያለው የግናዛቤ ክፍተት እንዲሁም በአካባቢው የሳር አቅርቦት አለመኖር ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታትም ግንዛቤ የመፍጠርና በክልሉ እንዲሁም በፌደራል መንግስት የሚተዳደሩ ፓርኮች ሳሮችን የሚያቀርቡበት አሰራር መፍጠር ላይ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው ቅርሱን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ነዋሪዎች የሚያነሱት አንዱ ጥያቄ የሳር ክዳን መወደድ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ ክልሉ በሚያስተዳድረው ማዜ ብሄራዊ ፓርክ በተወሰነ ቦታ ላይ ሳር ለማልማት ፕሮጀክት እየተነደፈ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

(ኢፕድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...