“ባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደሳምባና የደም ስር የሚታይ ነው” – ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም

Date:

ባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደ ሳምባና የደም ስር የሚታይ በመሆኑ ህልውናን ለማስጠበቅ የምንጠይቀውና የምናረጋግጠው ነው ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ወለድ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ገለጹ።

ወደር የሌለው የኢትዮጵያ የጦር ሜዳ ሜዳይ ተሸላሚ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማርያም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ሁለንተናዊ እድገቷ ተገትቷል።

የባሕር በር ለኢትዮጵያ እንደ መተንፈሻ ሳምባና የደም ስር የሚታይ በመሆኑ የመኖርና ያለመኖርን ጉዳይ ነው፤ ጥያቄው የልመና ሳይሆን የመብትና የህልውና ጥያቄ ነው ብለዋል።

እንደብርጋዴልር ጀነራል ተስፋዬ ገለጻ፤ የባሕር በር አልባ መሆን ሀገሪቱን ለውጭ ጥቃት በቀላሉ ተጋላጭ ከማድረጉም በላይ ጠንካራ የባሕር ኃይል እንዳይኖራት፤ የኢኮኖሚ ጫና እንዲከሰትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋቸው እየናረ እንዲሄድ አድርጓል።

በወቅቱ የነበሩ መሪዎች በግድየለሽነት አሰብን አሳልፈው ለኤርትራ በመስጠታቸው ዛሬ ለደረስንበት መከራ መዳረጋችንን ጠቅሰው፤ ኤርትራ ስትገነጠል የባሕር በር ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ በውጭ ኃይሎች በኩል ግፊት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይህ ታሪካዊ ስህተት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም፣ የአካልና የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉበትን ክብር ያሳጣ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የባህር በር ለማግኘት በመንግሥት በኩል የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች የሚደገፉ በመሆኑ፤ የእኛን መብት ሊያስከብርልን ማንም ከውጭ ስለማይመጣ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ታላቅ ሀገራዊ አጀንዳ ከመንግሥት ጎን ልንቆምና ልንሰለፍ ይገባል ብለዋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...