የአሜሪካ እና ቱርክ ፕሬዚዳንቶች በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ በኒዘርላንድስ ተወያዩ፡፡
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶሃን እና ዶናልድ ትራምፕ በተለይም በእስራኤል -ኢራን ጦርነት ዙሪያ ትኩረት ሰተው ተወያይተዋል።
የዶናልድ ትራምፕን የተኩስ አቁም ጥረትም አድንቀዋል ኤርዶሃን፡፡
በ ዘ ሄግ ኒዘርላንድስ እየተካሄደ ባለው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት (ኔቶ) ስብሰባ ላይ ነው መሪዎቹ ተገናኝተው በጦርነቱ ዙሪያ ያወሩት።
የአንካራው ኤርዶሃን በቴል አቢቭ እና ቴህራን መካከል ያለውን ጦርነት በተኩስ አቁም ለመቋጨት ትራም የተጫወቱትን ሚና በበጎ ተመልክተውታል፡፡
ምንም እንኳን እስራኤል እና ኢራን አንዳቸው በሌለኛው ላይ ክስ እያቀረቡ ጦርነቱን ሊያስቀጥሉት ቢችሉም ትራምፕ ለተኩስ አቁም በር ከፍተዋል፡፡
በጋዛ ስላለው ቀውስ እንዲሁም የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት በውይይት ስለመፍታት መሪዎቹ ተነጋግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
በ-ቢኒያም ካሴ
