ቼልሲ ሪያል ቤቲስን 4 ለ 1 በማሸነፍ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል።
ዛሬ ምሽት በተደረገው የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሪያል ቤቲሶች 1 ለ 0 እየመሩ ዕረፍት መውጣት ቢችሉም ቼልሲዎች ከዕረፍት መልስ ባስቆጠሯቸው 4 ግቦች ሻምፒዮናነቱን ተጎናፅፈዋል።
ሪያል ቤቲስን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ኤዛልዙሊ በ9 ደቂቃ ቢያስቆጥርም ቼልሲን አሸናፊ ያደረጉ ግቦችን ኢንዞ ፌርናንዴዝ፣ ጃክሰን 70ኛ፣ ጄደን ሳንቾ በ83ኛ እና ካይሴዶ በ91ኛ ደቃቂዎች ላይ አስቆጥረዋል።
የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ ዛሬ ምሽት የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ አራቱንም የአውሮፓ እግርኳስ ማኅበር የሚያዘጋጃቸው የክለብ ውድድሮች ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።
ሰማያዊዎቹ ከዚህ በፊት ዩኤፋ የሚያዘጋጃቸውን ሦስቱን ውድድሮች ማለትም ሻምፒየንስ ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና የሱፐር ካፕ አሸናፊዎች ዋንጫዎችን ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ዛሬ ምሽት የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን በማሸነፋቸው አራቱንም የዩኤፋ ታላላቅ የክለብ ውድድሮች ዋንጫ ያሸነፈ የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል።
