አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

Date:

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱንና አጠቃላይ ሀብቱን ከ14 ነጥብ 32 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱንም ገልጿል።

አሐዱ ባንክ አክሲዮን ማህበር 5ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፥ በዚህ ወቅት ሁለት አዳዲስ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በይፋ አስተዋውቋል፡፡

በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የተቀማጭ ገንዘቡን 10 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር ማድረሱንና ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ እድገት ማሳየቱን በመግለጫው አመለካቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ከ121 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መሰብሰቡን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያመላከተው ባንኩ፥ በደንበኞች ቁጥር በኩልም በሂሳብ ዓመቱ 252 ሺህ 530 አዳዲስ ደንበኞችን በመመዝገብ፣ አጠቃላይ የደንበኞቹን ቁጥር 1 ሚሊዮን 343 ሺህ 906 ማድረሱን ገልጿል።

በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት በዋና ዋና የአፈጻጸም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡንም ጠቁሞ፥ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ሁለት የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በይፋ አስተዋውቋል፡፡

ባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን ለማሳደግ “አሐዱ ለኩሉ” እና “ማኅደር” የተሰኙ ሁለት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ወደ ሥራ ማስገባቱንም በይፋ አስታውቋል።

ከሌሎች የእድገት እርምጃዎቹ መካከልም ሁለት የመሬት ውስጥ ወለሎች፣ የመሬት ወለልና 15 የላይኛ ወለሎች ያሉትን የንግድ ሕንፃ መግዛቱን ጠቅሷል።

በቀጣይም የደንበኞችን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ በዲጂታል ፈጠራና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዛሬ በሠጠው መግለጫ አስታውቋል።

በናርዶስ አለማየሁአሐዱ ባንክ ከታክስ በፊት 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...