ሊዊስ ስኬሊ በአርሰናል ቤት ያለውን ቆይታ ለ5 ተጨማሪ አመታት ዛሬ ረፋድ አራዝሟል ።
ከ8 አመቱ ጀምሮ በአርሰናል ማሰልጠኛ ማዕከል ያደገው ተጨዋቹ አሁን 18ኛ አመቱ ላይ ይገኛል ። አምና ፕሮፌሽናል ፊርማውን ሲያኖር በሳምንት 4,000 ፓውንድ እየተከፈለው ለ3 አመት የሚቆይ ነበር ። ይህ ውሉ በ2026 ይጠናቀቃል ።
ዛሬ ደሞዙ ይፋ ባይደረግም በርሱ እድሜ ላይ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንፃር ምርጥ ነው ተብሏል ።
መረጃዎች እንዳመላከቱት በሳምንት ከ40,000-60,000 ፓውንድ ይከፈለዋል ።
በዚህ እድሜ ትልቁን ደምዝ የሚያገኘው የፔዤው ዛይሪ ኤምሪ ኤምሪ ሲሆን በሳምንት 135ሺ ፓውንድ ያገኛል ።
የዩናይትዱ ሊኒ ዮሮ 115ሺ ፓውንድ እንዲሁም አርዳ ጉለር ከማድሪድ 84 ሺ ፓውንድ እየተከፈላቸው ከ1እስከ 3 ተቀምጠዋል ።
የሊዊስ ስኬሊ አዲስ ፊርማ ምርጥ 10 ወጣት ተከፋይ ውስጥ ባያስገባውም ከማድሪድ እይታ ውስጥ ከልሎታል ።
