የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አውሮፓውያን ትንንሽ አሳማዎች ናቸው ሲሉ ወረፉ።
አውሮፓውያን ዩክሬንን በመርዳት ጦርነቱ እንዳይቆም በማድረግ የሩሲያን ውድቀት የሚመኙ በማለት ፑቲን ተናግረዋል ።
አውሮፓውያን ከዚህ ቀደም በታሪክ ያጡትን ሁሉ አሁን ሩሲያን በማዳከም ለማካካስ አሰፍስፈዋል ፣ ይህ ግን የሚያዛልቅ አይሆንም ነው ያሉት ፑቲን።
ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር መደራደር ትፈልጋለች ፣ አሁን ያሉት ግን ያልበሰሉ ስለሆኑ አስቸጋሪ ናቸው ካሉ በኋላ የሩሲያ ጦር ምስጋና የሚገባዉ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ በዓለም እንደሩሲያ ያለ ወታደራዊ አቅም ያለው፣ በጦር ሜዳ የተፈተነ ብሎም ልምድ ያለው ሰራዊት የለም ሲሉ ፑቲን ወታደሮቻቸውን አሞካሽተዋል።
ፑቲን ከጦር ሚኒስትሮቻቸው ጋር ዓመታዊ ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው አውሮፓውያንን ክፉኛ የወቀሱት።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን መረን የለቀቀ ድጋፍ በማድረጋቸው ተጠያቂ ናቸውም ብለዋል።
ፑቲን ለጦር ሚኒስትሮቻቸው የሰጡት ማብራሪያ እና መግለጫ ለተቀናቃኞቻቸው ጥብቅ መልዕክት ያዘለ እንደሆነ ያሳብቃል ይላሉ ተንታኞች ።
ፖለቲኮ ዘግቦታል።
