ኢትዮጵያ እና ብራዚል ተፈራረሙ

Date:

ኢትዮጵያ እና ብራዚል በንግድ እና ግብርና ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን ያደረጉት ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮ- ብራዚል የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ላይ ነው።

ፎረሙ በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር ፣ የገበያ ትስስር መፍጠር እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድል በሮችን በመግክፈት የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በፎረሙ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቁልፍ በተባሉ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች እንደምትገኝ ገልፀዋል።

በዋናነትም በግብርና እና ግብርና ነክ ኢንዱስትሪዎች ፣ማኑፋክቸሪንግ እና ማዕድን፣ታዳሽ ኃይል እና ቴክኖሎጂ ፣ ቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ እየተሰራ መሆኑን ለብራዚል ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያም በስፋት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጋብዘዋል።

በተመሳሳይ በፎረሙ የተሳተፉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት እያሳየች መሆኑን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ ወደ ብራዚል ጥሬ ዕቃ ከመላክ ይልቅ እሴት በመጨመር ያመረተቻቸውን ምርቶች ትልካለች ብለዋል።

በፎረሙ በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ጆንዳሪዮ፣ በተለይም ግብርና እና ግብርና ነክ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያና፣ የንግዱ ማህበረሰብና ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ወደፊት የንግድ ትስስር እንዲፈጠርላቸው አስቻይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚኖራቸውን የንግድ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ይህ ፎረም ኢትዮጵያ ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት ለመግባት ለምታደርገው ጥረት እና በብሪክስ አባልነቷ ለምታገኘው የኢኮኖሚ ጥቅም ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ምርቶቿን ወደ ብራዚል በመላክ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ አጠናክራ እንድትሰራ ይረዳታል ተብሏል።
ሁሉቱም ሀገራት የብሪክስ አባል መሆናቸው ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...