እስራኤል  እስረኞች እንዳያመልጡ በማረሚያ ቤት ዙሪያ አዞዎችን ልታሰማራ ነው

Date:

በእስራኤል የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ኢዲት ሲልማን የተላለፈው አዲስ ውሳኔ በአገሪቱ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። ሚኒስትሯ አዞዎችን “ከዱር እንስሳት” ተፈጥሮአዊ ምድብ በመቀየር “በሰው እጅ የሚረቡ የዱር እንስሳት” በሚል እንዲመደቡ ፈርመዋል።

ይህ የህግ ማሻሻያ አዞዎች ለአገሪቱ የፀጥታ አካላት፣ በተለይም ለወህኒ ቤት ጥበቃ አገልግሎት እንዲውሉ ሙሉ በሙሉ በር ከፍቷል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ግቪር ያቀረቡትን “አዞዎችን በመጠቀም እስረኞች እንዳያመልጡ መከላከል” የሚል እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

እቅዱ በደቡባዊ እስራኤል በሚገኘውና በርካታ ፍልስጤማውያን ታሳሪዎች ባሉበት የኬትዚዮት ማረሚያ ቤት ላይ በሙከራ ደረጃ ይጀምራል ተብሏል።

ሚኒስትር ቤን-ግቪር ውሳኔውን ተከትሎ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ አዞ በገመድ ስቦ የያዘበትን በAI የተሰራ ፎቶ በመለጠፍ “ለማምለጥ እያሰባችሁ ነው? ድጋሚ አስቡበት!” የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይሁን እንጂ ውሳኔው ከፍተኛ ተቃውሞ እና ስጋት አስከትሏል። የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ዋና የህግ አማካሪ አዞዎችን ለዘመናዊ ወህኒ ቤት ጥበቃ መጠቀም ምንም አይነት ሙያዊ ቅድመ-ታሪክ የሌለው ተግባር ነው በማለት በፅኑ ቢያስጠነቅቁም ሚኒስትሯ ህጉን አፅድቀውታል።

በተመሳሳይ የእስራኤል የተፈጥሮ እና ፓርኮች ባለስልጣን ውሳኔውን አጥብቆ በመቃወም የዱር እንስሳትን ለሰው ልጅ የፀጥታ ጥበቃ ማሰማራት ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል።

ተቋሙ አክሎም አዞዎቹ ከማረሚያ ቤቱ ቢያመልጡ በህዝብ ደህንነት ላይ ከባድ አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት አዞዎችን ለመያዝ የነበረው የህግ እገዳ ቢነሳም፣ የወህኒ ቤት አስተዳደሩ እቅዱን በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን ወጪ፣ የሎጂስቲክስ እና የቴክኒክ ብቃት በጥናት ላይ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር …

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7...

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...