እናት ባንክ ከፍተኛውን የብሄራዊ ባንክ ሽልማት አሸነፈች

Date:

እናት ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ በሴቶች አካታች የባንክ አገልግሎት የምዘና መስፈርት ብቸኛና ቀዳሚ ባንክ በመባል ተሸለመች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት መሰረት እናት ባንክ የተሻለ ስራ በመስራቷ ከ30 የኢትዮጵያ ባንኮች የመጀመሪያና ብቸኛ ባንክ መሆኗ ተገልጿል።

ለሴቶች የተለየ የባንክ አገልግሎት ማቅረብ፣ በፈጠራ የተደገፈ የባንክ አሠራር መዘርጋት ብሎም ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የባንኮች ሁሉን አካታችነት የባንክ አገለግሎት መስፈርቶች ሲሆኑ እናት ባንክም እነዚህን መስፈርቶች በማሟላቷ ቀዳሚ ባንክ መባል ችላለች።

በእነዚህና መሰል ምክንያቶች እናት ባንክ ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች የባንክ አገልግሎት አሰራር ዘርግታ በመስራቷና ሌሎች ሴቶችን በንግዱ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያድርጉ ተግባራትን በማከናወኗ በተቀመጠው መለኪያ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተመዝግባለች።

በዚህም የእናት ባንክ ደንበኞችን፣ የቦርድ አባላቶችን፣ ባለ አክሲዮኖችን፣ አደራጆችን ብሎም ከፍተኛ አመራሮችን እና ሠራተኞች ባንኳ አመስግናለች።

ከይትባረክ ፌስቡክ ገፅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...