የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እግርኳስ በአሜሪካ በቅርብ አመታት ውስጥ ቁጥር አንድ ተወዳጅ ስፖርት እንደሚሆን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በሊጉ የመውረድ እና ማደግ ህግ እንዲተገበር ጠይቀው ስፖርቱ ተወዳጅ እንዲሆን ይረዳዋል በማለት ገልጸዋል።
“ እግርኳስ በአሜሪካ ቁጥር አንድ ስፖርት የመሆን አቅም አለው “ ሲሉ ፊፋ ለዚህ ግብ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ ተናግረዋል።
“ በጥቂት አመታት የአሜሪካ ሊግ ከአለም ምርጥ ሊጎች አንዱ ይሆናል “ ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ ለምን እንደሆነ መናገር እችላለሁ ምክንያቱም እኔ አሁን እዚህ ነኝ ብለዋል።
ስለ ክለቦች አለም ዋንጫ ያነሱት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ” ውድድሩን ተጨዋቾች ወደውታል “ ሲሉ ተናግረዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
