ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በፋብሪካ የተቀነባበረ  የበሬ ሥጋ ንግድ ተጀመረ

Date:

‘ራንቸርስ ፋይነስት’ የተባለው የኡጋንዳ የግል ሥጋ አቀናባሪ ኩባንያ፣ በየወሩ 20 ቶን የስቴክ፣ የቋሊማና የበግ ሥጋ ምርቶችን ለኢትዮጵያው ‘ዳይመንድ ሆቴልና ሬስቶራንት ግሩፕ’ ለማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።

​የኡጋንዳ ባለሥልጣናት ይህንን ስምምነት ለአገሪቱ የእንስሳት ዘርፍ ትልቅ እቅስቃሴና እሴት በመጨመር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተደረገ ስኬት ነው ብለውታል።

ጥሬ ሥጋን በኪሎ 4 ዶላር ከመሸጥ ይልቅ በማቀናበር እሴት ጨምሮ እስከ 50 ዶላር መሸጥ እንደሚቻልም ጠቅሰዋል።

​ኢትዮጵያ የተመረቱ የምግብ ምርቶች ገበያን እያሰፋች ሲሆን፣ በቅርቡ ከብራዚልና ከአሜሪካም መሰል የእንስሳትና የግብርና ምርቶችን ለማስገባት ፈቃድ መስጠቷ ይታወሳል።

ምንጭ:  ኡጋንዳ ናየል ፖስት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...