ዛሬ ምድር በከፍተኛ ፍጥነት እየዞረች ነው – ሳይንቲስቶች

Date:

ዛሬ ምድር በከፍተኛ ፍጥነት እየዞረች መሆኑን የገለጹት ሳይንቲስቶች፤ ቀኑ አጭሩ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት ምድር በከፍተኛ ፍጥነት እየዞረች ነው ያሉት ሳይንቲስቶቹ፤እ ሽክርክሪቱ ከበፊቱ በበለጠ ፍጥነት የሚካሄድ በመሆኑ ዛሬ ጁላይ 9 ቀን 2025 ዓ.ም በሰው ልጆች ታሪክ አጭር ቀን ሊሆን እንደሚችል አብራርተዋል።

በዚህም ዛሬን ጨምሮ በፈረንጆቹ ጁላይ 22 እና ኦገስት 5 ቀናቶቹ ከወትሮው በ1 ነጥብ 3 እና 1 ነጥብ 51 ሚሊ ሰከንዶች የሚያጥሩ እንደሚሆኑ ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡

ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፤ ይኼ ክስተት እ.ኤ.አ ከ2020 ጀምሮ የተስተዋለ ሲሆን፤ ጁን 5 ቀን 2024 ዓ.ም ከወትሮው በ1.66 ሚሊ ሰከንዶች ያጠረ ቀን መከሰቱ ተመዝግቧል፡፡

የክስተቱ ምክንያት አሁንም ድረስ በሳይንቲስቶች እየተጠና ነው ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...