ባለፈው ጥር ወር ወደ ስልጣን የመጡት ዶናልድ ትራምፕ ከወሰዷቸው አበይት ውሰኔዎች መካከል የ USAIDን ስራ መዝጋት ነው በዚህም በርካታ አገራት ያገኙ የነበረው ድጋፍ እንዲቋረጥ ሆኗል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የ2018 በጀቱን ለፓርላማ ያቀረበው መንግስት ለጤናው ዘርፍ ከራሱ ካዝና የመደበው በጀት እንዲጨምር አስገድዶታል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ በበጀት ንግግራቸው ወቅት ይሄን አረጋግጠዋል።
ስም ባይጠሩም አንዳንድ አገራት ድጋፍ በማቋረጣቸው መንግስት ለጤናው ዘርፍ በተለይ ለመድሃኒት ግዥ ከራሱ ከፍተኛ በጀት ለመያዝ ተገዷል ብለዋል።
በርግጥ አገራቱ ድጋፉን መልሰው እንደሚጀምሩ እየገለፁልን ነው ሲሉ አክለዋል።
ለ2018 በጀት አመት መንግስት ለጤና ዘርፍ በካፒታል ወጪ ከራሱ ቋት 32 ቢሊየን ብር መድቧል።
በተጨማሪ በእርዳታ 16 ቢሊየን እንደሚገኝ ነው የገለፀው።
ይህ ሁኔታ የ2017 በጀት ቀመር ላይ የተለየ ነበር። በ2017 በጀት አመት ለጤና ዘርፍ ተይዞ ከነበረው የካፒታል ወጪ እርዳታ 12 ነጥብ 6 ቢሊየን ከመንግስት ካዝና አራት ቢሊየን ብር ነበር።
ቅዳሜ ገበያ
