የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ፈተና ውጤት ዝቅተኛ የመሆኑ ምክንያት በጥናት ሊለይ ይገባል

Date:

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥር ዝቅተኛ የመሆኑ ምክንያት በጥናት ሊለይ እንደሚገባ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ አሳሰበ።

ቋሚ ኮሜቴው የትምህርት ሚኒስቴርን የ2018 ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በትምህር ሥርዓቱ የተደረገው ማሻሻያ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ እና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት ረገድ ውጤት ቢመዘገብበትም፣ የትምህርት ሥርዓቱ አሁንም መቶ በመቶ ከችግር መላቀቅ አልቻለም ተብሏል።

ከባለፉት ዓመታት አንፃር በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ቢጨምርም፣ ለፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ቁጥር አንፃር ሲታይ ግን ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከዓመት ዓመት ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱም ተጠቅሷል።

ባለፉት አራት ዓመታት በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያለውን ስብራት ለመጠገን ዘርፈ ብዙ ሪፎርም መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮችን መንስኤ ለይቶ ማውጣት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።

ebc

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...