የ25ኛዉ ሶፊ ማልት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጽያ አሸናፊዎች

Date:

25ኛዉ ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ የ10 ኪ.ሜ  ዉድድር ዛሬ በመዲናዋ በደመቀ ሁኔታ ሲከወን በኤሊት አትሌቶች ዉድድር  አትሌት ገረመዉ ድሉ  እና አትሌት መልክናት ዉዱ አሸናፊ መሆን ችለዋል።

በሴቶች ፍታው ዘርአይ 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ መሰለች አለማየሁ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛለች ፡፡

በወንዶች እየብ ሲመኝ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ድንቅ አለም አየለ ደግሞ 3ኛ  ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

መልክናት ውዱ የ2016 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን ውድድሩን ለ2ኛ ጊዜ አሸንፋለች፡፡

ዉድድሩን ላሸነፉት አትሌቶች የ4መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እና ዋንጫ ሲበረከትላቸዉ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዉ ላጠናቀቁ አትሌቶች ደግሞ የሁለት መቶ ሺህ እና የመቶ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በ25ኛዉ ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ ዉድድር ከ55ሺህ በላይ ተሳታፊዎች  ሲካፈሉበት ከ25 ሀገራት የተዉጣጡ  ከ250 በላይ ተሳታፊዎች ታድመዉበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...