የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንን ጎብኙ

Date:


የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉት ጉብኝት በአፍሪካ-ማሌዥያ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነውም ተብሏል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የኅብረቱ እና የማሌዥያ ትብብር ለሁለቱም አካላት ዕድገት አዳዲስ መንገዶችን ይከፍታል።

አክለውም በፈረንጆቹ 2024 የማሌዥያ እና የአፍሪካ ንግድ 7.5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን እና በሁለት ዓመታት ውስጥ ከ20 በመቶ በላይ ማደጉን ጠቅሰው፥ ይህም የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ያለውን ጠንካራ ግስጋሴ ማሳየ ነው ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ከ40 ሺህ የሚበልጡ ወጣት አፍሪካውያን በማሌዥያ ትምህርታቸውን መከታተላቸውንም አንስተው፤ ይህ ሌላው የአፍሪካ-ማሌዥያ ወዳጅነት ምሰሶ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በበኩላቸው የማሌዥያ-አፍሪካ ግንኙነት በንግድ፣ በአግሪ-ቢዝነስ እና በትምህርት እያደገ መምጣቱን አንስተው፤ ሁለቱም ወገኖች በተለያዩ መስኮች በሚያደርጉት ትብብር  ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...