የሲሚንቶ ፉብሪካዎች በግብዓት አቅርቦት ዙርያ ምክክር ተደረገ

Date:

የሲሚንቶ ፉብሪካዎች ምርታቸውን ማሳደግ በሚችሉበትና በሲሚንቶ ግብዓት አቅርቦት ዙርያ ምክክር መካሄዱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ገለጹ፡፡ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በስራ ላይ ያሉ የሲሚንቶ ፉብሪካዎች የሲሚንቶ ምርታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉን ጉዳዮችና የግብአት አቅርቦት ዙሪያ ከሲሚንቶ ፋብሪካ ኃላፊዎች እና የክልል ማዕድን ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡በውይይቱ ላይ በቅርቡ ስራ ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ያለው የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ መሳተፉን ጠቅሰዉ ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉ የግብአት አቅርቦት እንዲያገኝ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ አዲስ ለሚገነቡ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መደረግ ስላለበት ድጋፍ መወያየታቸዉንና በተለይ ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...