የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኦቻ ዳይሬክተር ጋር ተወያየ

Date:

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ በትግራይ ለተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች “ቁልፍ እና ዘላቂ መፍትሔው” በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት በሰላም ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ነው ሲሉ ተናገሩ።

አቶ አማኑኤል ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በ ሽረ እንዳስላሴ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የአፍሪካ ዳይሬክተር ከሆኑት ኪዮኮ ኦኖ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

የተፈናቀሉ ቤተሰቦች “ደህንነታቸውና ሰብዓዊ መብቶቻቸው ተጠብቆ” ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲችሉ የፕሪቶሪያን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያፍልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።


አቶ አማኑኤል አክለውም፣ “ተፈናቃዮች በሰላም እንዲመለሱ የታጠቁ ቡድኖች ከምዕራብ ትግራይ እና ከሌሎች ከተያዙ አካባቢዎች መውጣት አለባቸው፣ ሕገወጥ አስተዳደሮችም መፍረስ እንዲሁም አዳዲስ ሰፋሪዎች አካባቢውን መልቀቅ ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

እንደ አማኑኤል ገለጻ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች የድርጅቱ ኤጀንሲዎች “ሕዝብን አደጋ ላይ የሚጥሉ ወይም ከሰብዓዊ መርሆዎችና ከአሠራር ሂደቶች ጋር በማይስማሙ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ እንደማይሳተፉ” ለክልሉ ባለሥልጣናት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...