“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

Date:



አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር “የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል” በአዲስ አበባ ለመክፈት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ይህ ማዕከል በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን አካዳሚያዊ ትብብር፣ የባህል ልውውጥ እና የጋራ ምርምሮችን ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ማዕከሉ የዘመናትን የንግድና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጤት ነው።

የቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት ክቡር ዬ ሃይሊንግ፣ ማዕከሉ በቻይና መንግሥት ከሚደገፉ 25 ዓለም አቀፍ የምርምር ማዕከላት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ስትራቴጂካዊ እርምጃ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ አጋርነት ይበልጥ በማጠናከር፣ አዲስ የእውቀትና የልማት ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...

በአሰሪና ሰራተኛ የህግ ክርክር አዲስ የሰበር ውሳኔ ተላለፈ

ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት...