የአለም ምግብ ፕሮግራም አሁን ከሚረዷቸው ዜጎች ውስጥ ከ10 አንዱን ብቻ ለመደገፍ መገደዱን አስታወቀ

Date:

የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም  በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሶማሊያ ውስጥ በአስቸኳይ ጊዜ ምግብ እርዳታ የሚደግፈውን የሰዎች ቁጥር ከሁለት ሦስተኛ በላይ ለመቀነስ መገደዱን አስታውቋል።

ፕሮግራሙ ባቀረበው መረጃ መሠረት፣ በነሐሴ ወር 1.1 ሚሊዮን ሰዎችን ይደግፍ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ድጋፍ የሚያገኘው ቁጥር ወደ 350 ሺህ ሰዎች ዝቅ ይላል። ይህ ማለት ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው አስር ሰዎች መካከል፣ ድርጅቱ ድጋፍ መስጠት የሚችለው ለአንድ ሰው ብቻ መሆኑንም ተጠቁሟል።

የቅርብ ጊዜው የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ምደባ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ 4.4 ሚሊዮን የሚሆኑ ሶማሊያውያን በችግር ወይም ከዛ በላይ በሆነ የምግብ ዋስትና እጦት (IPC 3+) ውስጥ ይገኛሉ።

ከዚህም ውስጥ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉት በአስቸኳይ የረሃብ ደረጃ (IPC 4) ውስጥ ይገኛሉ፤ ይህም ቁጥር በስድስት ወራት ውስጥ በ50 በመቶ ጨምሯል።

የምግብ እጦት ችግር እየተባባሰ በመምጣቱ፣ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ሕፃናት መካከል 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑት በአጣዳፊ የምግብ እጦት ተጠቅተዋል።

አሁን ላይ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የድርጅቱ የሥነ-ምግብ ፕሮግራሞችም ቅነሳ የተደረገባቸው ሲሆን ድጋፍ እያገኙ ያሉት 180 ሺህ ሕፃናት ብቻ መሆናቸውን ተመላክቷል።

የአለም ምግብ ፕሮግራም እኤአ እስከ መጋቢት 2026 ባለው አስቸጋሪ ወቅት ለ800,000 ሰዎች አነስተኛውን የሕይወት አድን ሥራ ለመቀጠል በአስቸኳይ 98 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልገዋል። አስቸኳይ ተጨማሪ ገንዘብ ካልተገኘ፣ የሰብአዊ ፍላጎቶች እየጨመሩ በሄዱበት በዚህ ጊዜ የርዳታ ቅነሳው እየከፋ እንደሚሄድ አስጠንቅቋል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...