የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡርን በሙዚየምነት የማደራጀት ሥራ ተጀመረ

Date:

በድሬዳዋ የሚገኘውን የቀድሞ ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ግቢ ወደ ሙዚየምነት ለመቀየር በ9 ሚሊዮን ብር በጀት ጥናት እየተካሄደ እንደሆነ ተገልጿል።

የድሬዳዋ ደዋሌ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አየለ ወልደዮሐንስ እንደገለጹት፣ በቱሪዝም ሚኒስቴር በተመደበው 9 ሚልዮን ብር በጀት በግቢው ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ንብረቶችን ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ሥራ ይከናወናል።

በተጨማሪም፤ የለገሀር ተርሚናሉ በከተማ አስተዳደሩ በተመደበ 11 ሚሊዮን ብር በጀት በአዲስ መልክ የታደሰ ሲሆን፣ በቅርቡ የፈረንሳይ ሬስቶራንት ስራ ይጀምራል ተብሏል።

ተቋሙ በአሁኑ ወቅት 286 ሠራተኞችን በራሱ አቅም እያስተዳደረ እንደሆነ ያነሱት ሥራ አስኪያጁ፤ ከድሬዳዋ እስከ ጅቡቲ ጠረፍ ድረስም የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ከትራንስፖርት ጎን ለጎን ከከሰል ባቡር ውጪ ያገለገሉ ሁሉንም ባቡሮች፣ በቅርስነት የተመዘገቡ ቦታዎችን፣ ፎቶዎችን እና ወርክሾፖችን ያስጎበኛል።

አንጋፋው ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለድሬዳዋ ከተማ መመሥረት እና ወደ ኢትዮጵያ በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲገቡ ምክንያት መሆኑንም አቶ አየለ አስረድተዋል።

የቀድሞው ኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ታሪክ የጀመረው ከ130 ዓመታት በፊት እንደሆነ ይታወሳል፤ የመጀመሪያው የባቡር ሀዲድ በ1890 ዓ.ም. ከጅቡቲ እስከ ድሬዳዋ እንደተዘረጋ የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ።


ለአሐዱ ሬድዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...