የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1334/2016 መሠረት ብሔራዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ታስበው የሚውሉ በዓላት ተወስነዋል።
ግንቦት 20
ከወራት በፊት በፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን በወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየው ” ግንቦት 20 ” ብሔራዊ በዓልነቱ ቀርቷል።
በመሆኑም በዚህ ዕለት የሚዘጋ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አይኖርም / የሚዘጋ ስራ የለም።
