መቆጠብ ለማይችሉ መምህራን የኪራይ ቤት ተገንብቶ ይሰጣል

Date:


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንግድ ባንክ ጋር የተፈራረመው የመምህራን የቤት ቁጠባና ብድር አገልግሎት ጥሩ ቢሆንም በስምምነቱ መሰረት 25 በመቶ ቁጠባ የማድረግ አቅም እንደሌላቸው መምህራን ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመምህራን ስብሰባ “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ትበለፅጋለች” በሚል መሪ ሃሳብ ትናንት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ የንጋት ጮራ ትምህርት ቤት መምህር በውይይቱ ላይ፤ ከተማ አስተዳደሩ የመምህራንን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ያመቻቸው 25 በመቶ የቤት ግንባታ ቁጠባና 75 በመቶ የባንክ ብድር ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም በኑሮ ጫና ምክንያት 25 በመቶ መቆጠብ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

ዘጠኝ እና አሥር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ እየተከፈለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ ደመወዝ ላይ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 25 በመቶ ሊቆጥብ አይችልም፤ ሌላ አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህር፤ ከቤት ኪራይና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ ቤት ለማግኘት እንድንቆጠብ የተጠየቅነውን የ25 በመቶ ቁጠባ ለመክፈል ያዳግታል ብለዋል። ሌላ መፍትሄ ሊፈለግልን ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።

ለመምህራኑ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ መምህራን ያነሷቸው የቤት ጥያቄዎች ትክክልና ተገቢ ናቸው ብለዋል። ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተሰራው ስራም የቤት መስሪያ መሬት እና ዝቅተኛ ወለድ ያለው የብድር አገልግሎት የማመቻቸት ስራ እንደተከናወነ ተናግረዋል።

መምህራን ከዚህ በፊት በነበረ ስብሰባ ያነሱት ጥያቄ ለቤት ግንባታ የሚውል በነፃ መሬት ስጡን የሚል እንደነበር አንስተው፤በተጨማሪም የብድር አገልግሎት አመቻቹልን የሚል ጥያቄ ስለነበር ብድሩ መመቻቸቱን አብራርተዋል።

በዚህም 25 በመቶ መቆጠብ የሚችሉት እንዲቆጥቡ እና 75 በመቶ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ዕድል መመቻቸቱን ገልጸዋል።

ሆኖም መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

5 ሺህ ቤቶችን ለመምህራን ከኪራይ ወደ ባለቤትነት የማዘዋወር ስራ መሰራቱን አያይዘው አንስተዋል።
የመምህራን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በማህበር የማደራጀት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ በተሰራውም ስራ 350 ማህበራት ተደራጅተዋል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...