የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ትርፍ አገኝ

Date:

ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ47.57 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት በዚህ መግለጫ፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ  በዋና ዋና የስኬት መለኪያዎች ባንኩ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል ብለዋል።

ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች 648 ቢሊየን ብር ብድር  ሰጥቷል ሲሉ ፕሬዘዳንቱ አስረድተዋል።

ከ6 ዓመታት በፊት ባንኩ ይሰጥ ከነበረው ብድር 90 በመቶው ለመንግሥት ተቋማት የሚውል እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ዘንድሮ ግን ይህ አካሄድ ተቀይሮ 90 በመቶው (588 ቢሊየን ብር) ለግል ዘርፉ መሰጠቱን አስረድተዋል ።

በአጠቃላይ የተሰጠው ብድርም 1.64 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ከሪፖርቱ ላይ ተመልክተናል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓመቱ ውስጥ  ከ707.4 ቢሊየን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን፣አጠቃላይ ተቀማጩ 2.4 ትሪሊዮን ብር መድረሱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ባንኩ በበጀት አመቱ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊየን ዶላር  አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን፣ ባባለፉት ሁለት ዓመታት ያገኘው አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ መጠን 5.6 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል።

ባንኩ በቀጣዩ በጀት ዓመት 832 ቢሊየን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ፣አጠቃላይ ገቢውን ደግሞ 360 ቢሊየን ብር ለማድረስ እቅድ እንዳለው ተናግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...