የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት በአብዛኛው በባንክ ሴክተሩ ጤና ላይ የተመሰረተ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

Date:

በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የተረጋጋ እና የማይበገር መሆኑን ያስታወቀዉ ብሔራዊ ባንክ በዚህም ፋይናንስ ኢንዱስትሪዉን መቆጣጠራቸዉን ቀጥለዋል ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ በሐምሌ 2015 እና ሰኔ 2016 በፋይናንስ ሴክተሩ እና በሰፊው ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ እድገቶችን እና አደጋዎችን የሚመረምር ሁለተኛውን የኢትዮጵያ የፋይናንሺያል መረጋጋት ሪፖርት አቅርቧል ።

ማዕከላዊ ባንኩ በዚህ ሪፖርቱ እንደጠቀሰዉ በበጀት ዓመቱ በውጫዊ እና በአገር ውስጥ ባሉ ለውጦች ምክንያት የፋይናንስ ተቋማቱ የአደጋ መጠን መጨመርን የሚያመለክት ቢሆንም ስጋቶች በአብዛኛው መካከለኛ እና የተረጋጋ እንደነበሩ አስታውቋል ።

በአመቱ የፋይናንስ ሴክተሩን መረጋጋት የበለጠ ለማጠናከር ጠቃሚ ማሻሻያዎች ማድረጉን ያስታወቀዉ ብሔራዊ ባንክ የክፍት ገበያ ኦፕሬሽን (OMOs) አጠቃቀምን ፣ የምንዛሪ ተመን ሥርዓትን ነፃ ማድረግ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአዲስ መልክ በማዋቀርና በማደራጀት ማሻሻያ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል ብሏል።

የማይክሮ ፋይናንስ፣ የካፒታል ዕቃዎች ኪራይ እና የኢንሹራንስ ንግድ ዘርፎች ተንትነው በአጠቃላይ ጤናማ ሆነው የተገኙ ሲሆን በእነዚህ ዘርፎች ያለው አመለካከት በእድገት፣ በመረጋጋት እና በመቋቋም ረገድ አዎንታዊ ነው።

የካፒታል ዕቃዎች ኪራይ እና የኢንሹራንስ ንግድ ዘርፎች በአጠቃላይ ጤናማ ሆነው የተገኙ መሆናቸዉን እና በእነዚህ ዘርፎች በእድገት፣ በመረጋጋት እና በመቋቋም ረገድ ያለዉ አመለከታከት አዎንታዊ መሆናቸው ባንኩ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ በሚያወጣው ሪፖርቱ ላይ አመላክቷል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...