የኦሮሚያ ክልል ስድስት ዞኖች ብቻ እንዲኖሩት ተወሰነ

Date:

 

በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ላይ  የጸደቀው አዋጅ፤ ለዞኖች “ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ማዕቀፍ እና የመወሰን ስልጣን የሰጠ ነው” ተብሏል።

በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ” የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች፤ የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ” የወጣ እንደሆነ ተገልጿል።

እስከ ዛሬ በስራ ላይ የቆየው የክልሉ አደረጃጀት፤ የኦሮሚያ ክልልን በ21 ዞኖች ያዋቀረ ነበር።

አዲሱ አደረጃጀት ግን የኦሮሚያ ክልልን በአቅጣጫ ላይ በተመሰረቱ ዞኖች መልሶ የሚያዋቅር ይሆናል።

በዚህ መሰረት አዳዲሶቹ ስድስት ዞኖች፤ ፦
– ምስራቅ፣
– ምዕራብ፣
– ማዕከላዊ፣
– ደቡብ፣
– ደቡብ ምዕራብ
– ደቡብ ምስራቅ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

ይህን አደረጃጀት ስለያዘው አዋጅ ለጨፌ ኦሮሚያ አባላት ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ፤ የህግ ረቂቁ ” በክልሉ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ሪፎርሞችን ለማስቀጠል ” የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።

አዲሱ አዋጅ በስድስቱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ መስሪያ ቤቶችን ምንነት በግልጽ ያስቀመጠ መሆኑም ተገልጿል።

“ለዞኖች ከፍተኛ የመወሰን ስልጣንን ይሰጣል” የተባለለት ይህ አዋጅ፤ የክልሉ መንግስት የሚገነባውን ስርዓት “በህግ የተጠናከረ እንዲሆን ያደርጋል ” ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የድርድር ዕቅዷን ለአሜሪካ ልካ ምላሽ እየጠበቀች ነዉ

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ አገራቸው ሰባት ነጥብ...

የመልካም አዲስ ዓመት መግለጫ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ታደሰ ብሩ (ዶ/ር)

  ግዮን መጽሔት :-   ኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ እንኳን ለ2019 ዓ.ም....

‹‹የኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት ሕዝቧ ነው›› ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ

ግዮን መጽሔት :-  አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል ብቻ...