የኪ ሃውሲንግ 174 እድለኞች እጣ ወጥቶላቸዋል

Date:

የኪ ሃውሲንግ 4ተኛ ዙር የቤት እድለኞች የእጣ መለያ መርሐግብር ተካሂዷል።

በ83ሺህ145 ቅድመ ክፍያ እና ከ2000 ብር በሚጀምር ወርሃዊ ቁጠባ እየተካሄደ ያለው 4ተኛ እጣ የኪ ሃውሲንግ የቤት እድለኞች መለያ መርሐግብር በዛሬው እለት ባለ እድለኞቹ በተገኙበት ተካሄዷል።

ዛሬ በተካሄደው 4ተኛ እጣ የኪ ሃውሲንግ የቤት እድለኞች መለያ መርሐግብር የ174 ቤቶች እጣ ወጥቷል።

በዛሬው የቤት እጣ አወጥጥ ውስጥ ከሶስቱም ዙር የተወጣጡ ሰዎች መካተታቸው ተገልጿል።

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን “Economies of Scale” ላይ የተመሰረተ ሞዴል ቀርዖ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰባችንን ክፍሎች የቤት ባለቤት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ወደ ገበያው ከተቀላቀለ በአንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ መቶዎችን በአዲስ አበባ ስድስት ሳይቶች እና በባህርዳር ከተማ የቤት ባለቤት አድርጓል ተብሏል

በአሁኑ ሰዓትም 20ሺህ የሚደርሱ አባላት እንዳለው ገልጾ ኪ መንደር የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፈንታዬ በላይነህ የቦስተን ግማሽ ማራቶንን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ አሸነፈች

በ2026 የቦስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት...

ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት እውቅና ሰጠ

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ለክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ...

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...