የኮሜሳ ንግድ ትርዒትና በዛር

Date:

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በመዲናችን አዲስ አበባ 6ኛው የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን የኮሜሳ ሳምንት ንግድ ትርዒትና በዛር በስካይ ላይት ሆቴል ከሚያዝያ 27 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን መግቢያ በነጻ ነው፡፡

ይህ ልዩ ንግድ ትርዒትና ባዛር በኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በምስራቃዊና ዳቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ትብብር የሚካሄድ ነው፡፡

የንግድ ትርዒትና በዛር ዋና ዓላማም አህጉራዊ የነጋዴ ሴቶችንና ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን አቅም በመገንባት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና መልካም እድሎችንና አማራጮችን በማስፋት የሴት ነጋዴዎችንና ሥራ ፈጣሪዎችን ማብዛት ነው፡፡

በተጨማሪም በኮሜሳ አባል ሀገራትና በአፍሪካ ደረጃ ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስሮችን ማጠናከር፣ የንግድ ግንኙነቶችን ማጎልበት፣ ዕውቀት፣ ልምድና ቴክኖሎጂ ማሸጋገር እና አዳዲስ የቢዝነስ እይታዎችን በማበረታታት ቀጣይነት ያለውን ንግድና ኢንቨስትመመንት ትስስር ማጠናከር ነው፡፡

በዚህ የንግድ ትርዒትና ቢዝነስ ኮንፈራንስ ላይ ወደ 200 የሚጠጉ የጎንዮሽ የቢዝነስ ዉይይቶች ይካሄዳሉ፣ ከ200 በላይ ነጋዴ ሴቶችን ጨምሮ ከ400 በላይ ሴት ኢንቨስተሮችና የንግድ ተቋማት፣ ከ100 በላይ ትላልቅ አጋር ኩባንያዎች፣ ከ150 በላይ የሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎችና አዳዲስ ሴት ሥራ ፈጣሪ ነጋዴዎችም ይታደማሉ፡፡

ይህ የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ንግድ ትርዒትና ባዛር ለአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ወሳኝ የመሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን ከ600 ሚሊዮን በላይ የቀጠናው ሕዝብ የጋራ ገበያ ይፈጥራል፤ ከ260 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ጂዲፒ ወይም ቀጣናዊ ጠቅላላ ዓመታዊ ምርት እንዲንቀሳሰቀስም ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

በዚህ የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ ከሚሳተፉ የወጭ ሀገር ዜጎች ከ6000 በላይ ሰዎች በአካል፤ በ100 ሚሊዮኞች የሚቀጠሩ ሰዎች ደግሞ በሚዲያ አማካኝነት በኮርደር ልማት ሸብረቅ ባለ እንደ ስሟ ውብና አበባ የሆነችውን አዲስ አበባ ይገበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...