የኮሎኝ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪን የሚመክት አዲስ አንቲ ቦዲ አገኘ

Date:

የጀርመን የኮሎኝ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በኤች አይ ቪ ላይ አስገራሚ አቅም ያለው “04 A06” የተሰኘ አንቲቦዲ (የሰውነት መከላከያ ንጥረ ነገር) ማግኘታቸውን ይፋ አደረጉ።

ይህ ግኝት ለቫይረሱ ሁለንተናዊ ሕክምናን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

በሙከራ ጊዜ አዲሱ አንቲቦዲ ከሶስት መቶ በሚበልጡ የኤች አይ ቪ ዝርያዎች ላይ ሲሞከር ሁሉንም ማለት በሚቻል ደረጃ የማምከን አቅም አሳይቷል።

በተጨማሪም፣ የሰው ዘር በሆኑ አይጦች ላይ በተደረገው ጥናት፣ አንቲቦዲው የቫይረሱን መጠን ወደ “መገኘት ወደማይችል” (undetectable) ደረጃ ዝቅ በማድረግ ውጤታማነቱን አስመስክሯል።

አንቲቦዲው እንዴት ይሠራል? የ 04 A06 አንቲቦዲ ብዙ የኤች አይ ቪ ዝርያዎች በጋራ በሚጋሯት እና ለጥቃት ተጋላጭ በሆነችው “CD4 binding site” በተሰኘች የቫይረሱ ክፍል ላይ በማነጣጠር ይሰራል። ይህ ዘዴ የተለያዩ ዝርያዎችን የመዋጋት ሰፊ አቅም እንዲኖረው አስችሎታል፤ ይህም ሳይንቲስቶችን ሁለንተናዊ ሕክምናዎችን እና የመከላከያ ዘዴዎችን ለማዘጋጀት ያቀራርባቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...