የአለም ባንክ ለኬንያ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት 1.35 ቢሊየን ዶላር ሊያሰባስብ ሲሆን 375 ሚሊየን ዶላር በብድር መልክ ራሱ ባንኩ ሲሰጣት ከሌሎች አበዳሪዎች 900 ሚሊየን ዶላር ብድር እንድታገኝ ይረዳታል ተብሏል።
በተጨማሪ የነዳጅ ላኪዎች ድርጅት ወይም ኦፔክ ለቤት ግንባታው 75 ሚሊየን ዶላር ይሰጣል ተብሏል።
አለም ባንክ ኬንያ የ2 ሚሊየን ቤቶች እጥረት እንዳለባት አንስቶ ፍላጎቷ በአመት በ250,000 አባወራዎች እየጨመረ እንዳለ ነገር ግን የምታቀርበው ከ50,000 በታች እንደሆነ ገልጿል።
ብድሩ በመጪው ግንቦት ወር እንደሚፀድቅ ሲጠበቅ ዊሊያም ሩቶ በ2027 ሰርተው ለማጠናቀቅ ላቀዷቸው 1 ሚሊየን ቤቶችም ተስፋ የሰጠ ሆኗል።
ዘገባው የኬንያንስ ነው።
@TikvahethMagazine
