የጥናት እና የምርምር ውጤቶች እውነተኛነት ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ዋለ

Date:

ተማሪዎች የመመሪቂያ ፅሁፋቸው እውነተኛ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ አለመሆኑን የሚያረጋገጥ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ማዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የጥናት እና የምርምር ውጤቶች በሰው የተሰሩ መሆናቸውን የመለየት ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተሰራ የጥናት እና የምርምር ውጤት ውድቅ እየተደረገ መሆኑ አመላክቷል፡፡

ዘመን የሚያመጣቸውን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች አለመጠቀም እንደማይቻል የሚናገሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር)፤ “ዘመኑ ያመጣቸው ቴክሎጂዎችን ግን በሙሉ ያለ ጥንቃቄ አገልግሎት ላይ ማዋለት ተገቢነት የሌለው ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጥናት እና የምርምር ውጤቶች በተማሪዎች የተሰሩ መሆናቸውን የመለየት ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩም ሲሆን፤ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም የጥናት ውጤቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎ የተሰራ ከሆነ ውድቅ እንዲሆን የሚደረግበት አግባብ  መኖሩን አክለው ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የጥናት እና የምርምር ውጤቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አለመሰራታቸውን በሶፍትዌሮች በመታገዝ የመለየት ሥራ እያከናውኑ የሚገኙ ቢኖሩም፤ ሌሎችም ይህንን ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በዚህም ተቋማት ‘በቴክኖሎጂ አጠቃቀመ ረገድ ከዘመኑ ጋር አብረው እንዴት መጓዝ አለባቸው?’ በሚለው ጉዳይ ላይ ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

“የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ከመስፋፋቱ እና የዜጎች ቴክኖሎጂን ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሆኑ፤ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያለው ተጠቃሚነት ላይ ክትትል ማከናወን እንደሚገባ ታምኖበታል” ሲሉም ዶ/ር ኤባ ተናግረዋል፡፡

አክለውም የተማሪዎች የመመረቂያ እና የተለያዩ የምርምር ውጤት ላይ በቴክኖሎጂ የተሰሩ አለመሆናቸውን ለመለየት ጥረቶች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም “የሚቀርቡት የምርምር እና የጥናት ጹሁፎችን ላይ በተክኖሎጂ አማካኝነት የሚጣራበት ሁኔታ አለ” ያሉ ሲሆን፤ “በቀጣይም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ በስፋት ሊሰራበት ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...