የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያሸነፉትን የፊፋ የሰላም ሽልማት ተከትሎ ክስ ቀርቦባቸዋል።
ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የቀረበባቸው ክስ የፊፋን የፖለቲካ ገለልተኝነት ግዴታ በተደጋጋሚ ጥሰዋል በሚል መሆኑ ተገልጿል።
ቅሬታውን ለፊፋ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ያቀረበው ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም የሽልማቱ ሂደት ላይ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቋል።
ፕሬዚዳንቱ የሰላም ሽልማቱን ሲያዘጋጁ የተቋሙን ኮሚቴ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንቱን አለማማከራቸው ሲገለፅ ነበር።
