ዩቲዩብ “በብዛት ለሚመረቱ” እና “ተደጋጋሚ” ይዘቶች ክፍያ መፈጸም ሊያቆም ነው

Date:



ግዙፉ የቪድዮ ማሰራጫ መድረክ ዩቲዩብ፤ “በብዛት የተመረቱ” እና “ተደጋጋሚ” ቪድዮዎችን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከማስታወቂያ ገቢ መጋራት ስርዓት እንደሚያስወጣ አስታወቀ።

ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ ሰው ሠራሽ አስተውህሎትን (ኤአይ) በመጠቀም የሚሰሩ ይዘቶችን ከዩቲዩብ የክፍያ ስርዓት እንደሚያስወጣ ተገምቷል።

ዩቲዩብ ይፋ ባደረገው አዲስ ፖሊሲ ከሚቀጥለው ሳምንት ሐምሌ 8/2017 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ሁለት ማሻሻያዎችን አስተዋውቋል።

የመጀመሪያው ማሻሻያ ይዘት ፈጣሪዎች “የተጋለጠ ቆዳ” የሚታይበት ማስታወቂያ በቪድዮዎቻቸው ላይ እንዳይታይ ማድረግ የሚችሉበትን አማራጭ ያስወገደ ነው።

ይህ አማራጭ ይዘት ፈጣሪዎች በሚለቁት ቪድዮ የሰውነት ክፍሎች የተጋለጡበት ማስታወቂያ በይዘቶቻቸው ላይ እንዳይተላለፍ ለመገደብ ይጠቀሙበት ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...