ጄኔራል ታመነ ድልነሳው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

Date:


ኢትዮጵያ ካፈራቻቸዉ ምርጥ ጄኔራሎች አንዱ ሰለነበሩ ሐገራችንን በሐይል ለመደፈር የመጡበንን ጠላቶች በመደምሰ ድል አስመዘገበዉ ደማቅ ታሪክ ከሰሩት የቀድሞ ጄኔራሎች ዉስጥ ጄኔራል ታመነ ድልነሳው አንዱ ነበሩ ::


ለሀገራቸው በዋሉት ውለታ ከወታደራዊ አዛዠነት በተጨማሪ በዉጭ ጉዳይ ሚ/ር ከሚኒተሪ አታሸነነት እሰከ አምባሳደርነት ሙሉ ህይወታቸውን ለሀገራቸው የሰጡ ጀግና ናቸዉ።


ጀግና አዋጊና ተዋጊ የጦር መሪና ድፕሎማቱ ጄኔራል ታመነ
ድልነሳዉ ሠኞ (Monday) April 21 ለረጅም ጊዜ በስደት በኖሩበት በለንደን ከተማ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል::


በበርካታ የጦር ሜዳ ውጊያዎች ተሳትፈው የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የህዝብን ነፃነት ያስከበሩና ደማቅ ድል ያሰመዘገቡት ብርጋዲየር ጄኔራል ታመነ ድልነሳዉ የቀብር ሥርአታቸዉ የሚፈፀመው ለረዠም አመት በስደት በኖሩበት በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ መሆኑን ቤተሠቦቻቸው ገልፀውልኛል ።


ብሔራዊ ስሜት የታጠቁ ፡፡ የሀገር ክብር፡፡ የዜግነት ኩራትን የተረዱት፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ ተቆርቋሪና ምርኩዙ በመሆን ከኔ ጋር አብረዉ በየ ኮለጁና በዮኬ ዮኒቨርሰቲወች እየተዘዋወሩ ኢግዚቨሸኖችን አሳይተዋል።


የሀገር ፍቅር አቀንቃኝ ጀኔራል ታመነ ድልነሳዉ የኢትዮጵያ ፣ ባህል የጥንታዊነት ታሪክ ተንተኝ የአርበኝነትን አዋጅ ነጋሪም ነበሩ ::
ነፍስ ይማር ::


የኢትዮጵያ ቅርሰ ማበልፀጊያ ማሕበር ጄኔራል ታመነ ድልነሳው ከዚህ አለም በሞት መለየት የተሠማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን
ለመላዉ ቤተሰቦቻቸዉና ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሙሉ መፅናቱን እንዲሠጥልን ፈጣሪን እንለምናለን።

አለባቸዉ ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...