ሂውማን ራይትስ ዎች ትራምፕን ክፉኛ ነቀፈ

Date:

የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት (Human Rights Watch) ረቡዕ ዕለት ባወጣው ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ሪፖርቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ምሰሶዎች እየናዱ ነው ሲል አስጠነቀቀ።

ድርጅቱ ለዚህ በምክንያትነት የጠቀሰው የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት በስደተኞች ላይ የወሰዱትን ጠንካራ እርምጃ፣ በምርጫ መብቶች ላይ የተጋረጡ ዛቻዎችንና ሌሎች ፖሊሲዎቻቸውን ነው።

የሂውማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ፊሊፕ ቦሎፒዮን እንደጻፉት ከሆነ፣ ዋሽንግተን በአሁኑ ወቅት እንደ ሩሲያና ቻይና ያሉ አገራት ሰብዓዊ መብቶችን እንዲያዳክሙ መንገድ እየጠረገች ትገኛለች።

ቦሎፒዮን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፡- “በአሜሪካ ውስጥ እጅግ ጠላትነት የነገሰበት አካባቢና የዲሞክራሲ ጥራት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ መሆኑን እያየን ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም ዳይሬክተሩ በሪፖርቱ ላይ እንደገለጹት፣ የትራምፕ አስተዳደር በዘረኝነት ላይ በተመሰረቱ አመለካከቶች ላይ የሚደገፍና “ከነጭ ብሔረተኝነት (white nationalist) አስተሳሰብ ጋር የሚገጣጠሙ ፖሊሲዎችንና ንግግሮችን የሚያራምድ ነው” ሲሉ ከስሰዋል።

ቦሎፒዮን በሪፖርታቸው ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች በከፍተኛ ሁኔታ ተችተዋል፦

  • በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የሚፈጸመው አዋራጅ አያያዝ።
  • በሚኒያፖሊስ የተፈጸመው የሁለት ሰዎች ግድያ።
  • በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታው ወደሚታወቀው የኤል ሳልቫዶር “ሜጋ-እስር ቤት” ተለይተው መላካቸው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...