አቶ ግርማ ዋቄ የኡጋንዳ አየር መንገድን እንዲመሩ ሊሾሙ እንደሚችሉ ተገለፀ

Date:

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የኡጋንዳ አየር መንገድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጄኒፈር ባሙቱራኪን ከኃላፊነታቸው ማሰናበታቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዋቄ ተተኪ ሊሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።

ይህ የአመራር ለውጥ የተሰማው በአየር መንገዱ ውስጥ በግዥና በአስተዳደር ረገድ የታዩ ጉድለቶችን መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ እየመረመረ ባለበት ወቅት ሲሆን፤ የኡጋንዳ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት እና የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የፀረ-ሙስና ግብረ ኃይል በአየር መንገዱ የግዥ፣ የባንክ፣ የቲኬት ሽያጭና የአውሮፕላን ግዥ ሰነዶች ላይ ጥብቅ ምርመራ እያካሄዱ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ጄኒፈር ባሙቱራኪ ስለመሰናበታቸው የሚወጡ ዘገባዎች “ሐሰት ናቸው” ሲሉ ለቅርብ ወዳጆቻቸው ቢገልጹም፣ በአየር መንገዱ ውስጥ የአመራር ለውጥ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ታውቋል።

የኡጋንዳ መንግሥት አቶ ግርማ’ን ወደ አመራርነት ለማምጣት ማሰቡ አየር መንገዱን ከተጋረጠበት ኪሳራ ለማውጣትና እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ ለማድረግ ካለው ፍላጎት የመነጨ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ግርማ ዋቄ ኢትዮጵያ አየር መንገድን እኤአ ከ2004 እስከ 2011 በመምራት ለዛሬው ዕድገት መሠረት የጣሉ አንጋፋ መሪ መሆናቸው ይነገራል።

በአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን ሰፊ ልምድ ተጠቅመው አየር መንገዱን ወደ ትርፋማነት ሊያሸጋግሩ ይችላሉ ተብሎ የሚታመን ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው መሪ መሆናቸው በአሁኑ ወቅት በአየር መንገዱ ላይ ለታየው የአስተዳደር ችግር እንደ “መፍትሔ” ተደርገው እንዲታዩ አድርጓቸዋል።

የኡጋንዳ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳን ገቢው እያደገ ቢመጣም አሁንም ከፍተኛ የኪሳራ ጫና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለይም ወደ ለንደን ጋትዊክ የሚደረገው በረራ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ አየር መንገዱን በብቃት ሊመራ የሚችል ልምድ ያለው መሪ መፈለጉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...