” ለ11,639 መምህራን በሙሉና በከፊል አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ አልተከፈለም “

Date:

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ መምህራን በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ባለመፈጸሙ፣ በተለይ በኮሬ ዞን መምህራን የዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና “አንሰጥም” ብለው ሥራ ማቆማቸውን ገለጹ።

የክልሉ መምህራን ማህበር በአራት ዞኖች ከ11 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ መምህራን ክፍያው ሙሉ በሙሉና በከፊል አለመፈጸሙን አሳውቆናል።

መምህራኑ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው በማህበራቸው ጭምር በተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረብ 10 ወራት ጠብቀው አለመከፈሉን ገልጸው፣ ” ተማሪዎችን ፈተና አንፈትንም ” ብለው ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን  ተናግረዋል።

ነዋሪዎችም ፣ ልጆቻቸው ለማጠቃለያ ፈተና አለመቀመጣቸውን ገልጸዋል።

ለመምህራኑ ቅሬታ  ምላሽ የጠየቃቸው የኮሬ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ፣ ቅሬታቸው እውነተኛ መሆኑን አምነው፣ ” ባለፈው 50% ከፍለናል። ቀሪውን 50% ፈልገን በቀጣይ ልንከፍል ለውይይት ከተቀመጡት ጋር ተስማምተናል ” ብለዋል።

የመምህራኑን ሥራ ማቆም በተመለከተ ደግሞ “ወደ ሥራ እንዲመለሱ መግባባት ላይ ደርሰናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ሲጀመር ሙሉ ደመመዝ ለምን አልተከፈላቸውም ተብለዉ  ሲጠየቁ፣ ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ገንዘብ እንዳልተገኘ ገልጸው፣ ” ያገኘነውን 50% ከፍለናል። 50% ይቀራቸዋል። ቀሪውን ስናገኝ እንከፍላለን ብለን ተስማምተናል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ አስተዳዳሪው ” ስምምነት ላይ ደርሰናል ” ማለታቸውን መምህራኑ ውድቅ አድርገውታል።

” ሰኔ 25 ከሰዓት መምህራንን ስብሰባ ተጠርተው ብዙዎቹ አልገቡም አንድ እና ሁለት መምህራን ብቻ ከየትምህርት ቤቱ ተልዕኮ ተቀብለው በተገኙበት ‘ሁሉም ተስማምተዋል’ የሚለው የተሳሳተ መረጃ ነው ” ባይ ናቸው።

” መጀመሪያ በጥር ወር በሙያ ማህበራችን በኩል ጥያቄ ስናቀርብ ቆይተን በኋላ ዞኑ ያቀረብነውን ጥያቄ ላለመቀበል አሻፈረኝ በማለቱ የአንደኛ ሴሚስተር ፎርጅድ ውጤት ሰርተው ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ ስለላኩ አሁን ደግሞ ፈተናውን ሳንፈትን ከቀረን ህብረተሰቡም ግንዛቤ እንዲኖረው ፈልገን አልፈተንም ” ብለዋል።

በተያያዘ፥ የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ በሰጡን ቃል፦
– በጌዲኦ ዞን 4,228፣
– አሪ ዞን 4,434
– ኮሬ ዞን 2,070 
– በኧሌ ዞን 907፣ በድምሩ 11 ሺሕ 639 መምህራን ሙሉ በሙሉና በከፊል መንግስት በመስከረም ወር 2018 ዓ/ም የፈቀደው አዲሱ ጭማሪ እስከዛሬ አልተከፈላቸውም ብለዋል።

የኮሬ እና ኧሌ ዞን የሚቀራቸው 50% ክፍያ ሲሆን፣ በጌዲኦ እና አሪ ዞን የሚገኙ 8 ሺሕ 112 መምህራን ሙሉ ጭማሪው አልከፈላቸውም ብለዋል።

50 በመቶ ክፍያ ከተፈጸመላቸው መካከል የሆኑት የኮሬ ዞን መምህራን፣ “‘ሙሉው ካልተከፈለን ተማሪዎችን አንፈትንም’ አሉ፤ እኛም ተግባብተው ችግሩን እንዲፈቱ ጥረት አድርገናል። የዞኑ አስተዳዳሪም፣ 50%ቱንም ተበድረን ነው የከፈልነው፣ ቀሪውን እንከፍላለን” ነው የሚሉት ብለዋል።

” ከቀናት በፊት ተማሪዎች ድንጋይ ይዘው በአስተዳደሩ፣ በመምህራን ማህበር ሁከት ለመፍጠር ሞክረው በፖሊስ ነው የቆመው ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ” ውጥረቱ የተነሳው የክልሉ መምህራን ማህበር ጉዳዩን ቀድሞ ለሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቅም በወቅቱ መፍትሄ ሳይሰጠው በመቆየቱ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

አሁንም ክፍያው እንዲፈጸም አሳስበዋል።

ምላሽ ለማግኘት ወደ ክልሉ ት/ቢሮ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ ጥረቱ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...