ሲፒጄ መንግስት በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱ የወንጀል ክሶች በሙሉ እንዲነሱ ጠየቀ

Date:


 አለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ለሦስት ሳምንታት ያህል በእስር ላይ የነበሩት የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ አርታኢ ትዕግሥት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው ከእስር መፈታታቸውን በአዎንታ እንደተቀበለው መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ተቋሙ በመግለጫው በጋዜጠኞቹ መፈታት መደሰቱን ገልፆ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱ የወንጀል ክሶችን ሙሉ በሙሉ እንዲያነሱ እና የፍትህ ስርዓቱም የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር ጠይቋል።

ጋዜጠኞቹ ከእስር የተለቀቁት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት፤ በ50 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማፅናቱን ተከትሎ ነው።

በዚህም የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን እና ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው ከ21 ቀናት እስር በኋላ መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት አከባቢ መለቀቃቸውን ጣቢያው አስታውቆ ነበር።

ጋዜጠኞቹ ነሐሴ 28/2017 ለእስር የተዳረጉት ነሀሴ 24 ቀን 2017፣ በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ያቀረቡት የህክምና ባለሙያዎች ፣ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠውን መፍትሄ ሰርኩላር በመጥቀስ፣ እንዴት እንደሚመለከቱት የሚጠይቅ ዜና ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ነው።

የዜናና ፕሮግራም ሀላፊው እሸቴ አሰፋ ከጋዜጠኛ ምንታምር ፀጋው ጋር በዕለቱ ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቢሮ ከተወሰዱ በኋላ ቃላቸውን ሰጥተው ተለቀዋል።

የጋዜጠኞቹን እስር ተከትሎ የዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) የሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ባልደረባዎች የሆኑት ሪፖርተር ምንታምር ፀጋው እና አርታኢ ትዕግስት ዘሪሁን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ መጠየቁ ይታወሳል።

በወቅቱ የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “የኢትዮጵያ ህዝብ በጤና ዙሪያ የሚቀርቡ ገለልተኛ ዘገባዎችን ማግኘቱ ወሳኝ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም “ባለሥልጣናት በዚህ ጉዳይ ላይ በሳንሱር እና በቁጥጥር ምላሽ መስጠታቸው እጅግ አሳሳቢ ነው” ሲሉ ገልፀው ነበር። አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...