የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪና የአበል ክፍያ ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለክልሎችና ለከተማ መስተዳድሮች ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑ መኩሪያ ኃይሌ፣ ለሁሉም የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊዎች ባስተላለፉት መመሪያ፣ የደሞዝ ማስተካከያው የተደረገው መንግስት የመክፈል አቅም ኖሮት ሳይሆን፣ የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ስለሚያውቅ ነዉ ሲሉ አስረድተዋል።
ኮሚሽነሩ በተለይ ለክልሎች እና ለአንዳንድ አካባቢዎች በሰጡት ጥብቅ ማሳሰቢያ “ምንአልባት አንዳንድ አካባቢዎች በዚህ ወር ካልደረሰ ያለውን ማንኛውንም ጫና ተቋቁማችሁ ለሰራተኛው ከዚህ ወር ጀምሮ አዲሱን የመግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል እንዳለባቸው” ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ትላንት መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።
CapitalNews
