ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

Date:

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም በነበሩት ሶስት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚገኘው የቴሌኮም ድርጅቱ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን የኬንያ ሺሊንግ በካፒታል መልክ ማፍሰሱን ገለጸ።

ድርጅቱ ባወጣው አዲስ ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሰው ቅርንጫፉ ያደረገው ጠቅላላ የፋይናንስ አስተዋፅኦ ባለፈው መጋቢት ወር ከነበረበት 158.2 ቢሊዮን ሺሊንግ (1.223 ቢሊዮን ዶላር)፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ወደ 159.6 ቢሊዮን ሺሊንግ (1.234 ቢሊዮን ዶላር) አድጓል።

ይህ የካፒታል ጭማሪ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ባለው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ከፍተኛ ትኩረትና ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል።

ኩባንያው ይህንን ስራ የሚከውነው ከዋናው ባለድርሻ ቮዳኮም፣ ከሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን፣ ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት እና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን  ጋር በጋራ በመሆን ነው።

ይህ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ድርጅቱ በአገሪቱ የሚያደርገውን የኔትወርክ ማስፋፊያ፣ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻል እና የደንበኞችን ቁጥር የማሳደግ ስራ በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሚረዳው መሆኑ ተመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው...

ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሥራ ቡድን ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን...

የጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ 28 የውጭ ዜጋ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ጋር ማስተሳሰሩን ገለጸ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጎንደር ቃል-ኪዳን ቤተሰብ መርሃ-ግብር አማካኝነት በዘንድሮው ዓመት...

የሕግ ተማሪዎቹ አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት...