“ሺ ጂምፒንግ ምርጥ መሪ ነው!”- ትራምፕ

Date:


አሜሪካና ቻይና ተፎካካሪ ሳይሆኑ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ናቸው አሉ ፕሬዝዳንት ሺ ጂምፒንግ

የቻይናው መሪ ሺ ጂምፒንግ በቤጂንግ ታላቁ የህዝብ አዳራሽ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል፥

ደማቅ በነበረው በዚህ ስነስርአት ላይ መሪዎቹ እጅ ለእጅ ተጨባብጨዉ የአቀባበል ስነስርአቱን በቅደም ተከተል ሲፈፅሙ ታይተዋል፤

በዚህም ወቅት የቻይናው መሪ ሺ ተፎካካሪ አትበሉን እኛና አሜሪካ አጋርነት ያለን ሀገራት ነን ብለዋል።

ትራምፕ በበኩላቸው ሺ ታላቅና ምርጥ መሪ ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል!

የሁለቱ ሀያላን ሀገራት ግንኙንት ከምንጊዜውም በላይ የተሻለ ደረጃ ላይ ነውም ብለዋል ትራምፕ።

መሪዎቹ ከእንኳን ደህና መጡ ስነስርዓት መጠናቀቅ ተከትሎ ፥ አመሻሽ ላይ በዋና ዋና ጉዳዮች ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምግባረ-መልካሙ ኢትዮጵያዊ

ስለሺ መንገሻ - ከ1934 እስከ 2018 ዓ.ም ሠሎሞን ለማ ገመቹ. ግዮን...

ትራምፕ ለኔታንያሁ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ...

ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ...

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ከዓመታዊ የትርፍ 90 በመቶውን እንዲያከፋፍሉ ሊደረግ ነው

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ተብለው የሚቋቋሙ ፈንዶች ከዓመት ትርፋቸው ቢያንስ...