የአሜሪካ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች በኢትዮጵያ ላይ የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁ

Date:

በአሜሪካ የሚገኙ የፀሐይ ብርሃን ኃይል አምራቾች፣ የቻይና ኩባንያዎች የአሜሪካን የታሪፍ ቀረጥ ለማምለጥ ምርቶቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል እያሳለፉ ነው በሚል የንግድ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ባለስልጣናት ጥያቄ ማቅረባቸው ታዉቋል።

ኩባንያዎቹ ለአሜሪካ የንግድ ሚኒስቴር ባስገቡት አቤቱታ፣ “ቶዮ” እና “ኦሪጅን ሶላር ማንፋክቸሪንግ” የተባሉ የጃፓን ኩባንያዎች በቻይና የተሰሩ ግብዓቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ የሶላር ሴሎችን እንደሚያመርቱ ገልጸዋል። እነዚህም ምርቶች በኢትዮጵያ ወይም በቬትናም ተገጣጥመው ወደ አሜሪካ እንደሚላኩ ተጠቁሟል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2025 አጋማሽ ላይ የጀመረው የኢትዮጵያ የሶላር ምርቶች ወደ አሜሪካ የመላክ ሂደት፣ እስከ ዓመቱ መጨረሻ 300 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰባተኛዋ ከፍተኛ የሶላር ምርት ወደ አሜሪካ ላኪ ሀገር አድርጓታል።

አቤቱታውን ካቀረቡት መካከል “ፈርስት ሶላር” እና የደቡብ ኮሪያው “ኪውሴልስ” የሚገኙበት ሲሆን፣ ኩባንያዎቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በአሜሪካ ፋብሪካዎች ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸውንና ይህ “ህገ-ወጥ የታሪፍ ማምለጫ መንገድ” እድገታችንን ያደናቅፋል ሲሉ ተከራክረዋል።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም መሰል እርምጃዎችን በቻይና፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ካምቦዲያ እና ቬትናም ምርቶች ላይ መውሰዷ ይታወሳል። የንግድ ሚኒስቴሩ የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...