Home ልዩ ልዩ ዜና በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ስም የተሰየመው የሮያሊቲ ክፍያ ማስገኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በተወዳጁ የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ ስም የተዘጋጀው የሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በይፋ ተዋውቋል።

ሥርዓቱ ኤልያስ መልካ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሮያሊቲ መሰብሰቢያ ወይም (EMEMRC) የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነው።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብን አስመልክቶ በጋራ ያዘጋጁትን የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር ለማፅደቅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቀረበለትን ቀመር ለማፅደቅ ከሚዲያ አመራሮችና ከፈጠራ ባለሙዎች ጋር እየተወያየ ሲሆን፥ ተቋማት የሚከፍሉት የሮያሊቲ ክፍያ የገቢ አቅማቸውን መሰረት በማድረግ 24 ሠአት የሙዚቃ ውጤቶችን ይጠቀማሉ ተብሏል።

የሙዚቃ ተጠቃሚዎች በዓመትና በጊዜያዊነት ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉም ተሰምቷል።

ለአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቀረበው ቀመር መሰረት ተቋማቱ በ24 ሠአት ውስጥ 360 እነዲሁም በዓመት ደግሞ 131 ሺህ 400 ሙዚቃዎችን እንደሚያጫውቱ ተመላክቷል።

የሙዚቃ ባለሙያውም በተጫወተለት የሙዚቃ መጠን የሚከፈለው ሲሆን፥ ባለስልጣኑና ሁለቱ ማህበራት በዛሬው ዕለት የሮያሊቲ ክፍያ ቀመርን ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ዘግቧል።