“ቴሌ ብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ” 2017 በደማቅ ስነስርዓት ተከፈተ

Date:

‘በቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ’ ላይ ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ እንዳቀረቡ ሰምተናል።

የኤክስፖው አዘጋጅ ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን እንደገለጸው እስከዛሬ ከተደረጉ የንግድ ትርኢቶች የተለየ እና ልዩ የሚያደርጉት በርካታ ዝግጅቶች አሉት ።

ከንግድ ተቋማት በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ልዩ ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች በመስጠት የአካል ጉዳተኞች መንደር በኤክስፖው ተካቷል።

በዚህ መንደር በአካል ጉዳተኞች የተመረቱ ምርቶች ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ አካል ጉዳተኞች በኪነጥበብ ዘርፍ የተለያዩ የመድረክ ስራዎችን አቅርበዋል።

እንዲሁም በኤክስፖው ላይ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጋር በመተባበር የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በልዩ ሁኔታ የተዋወቀ ሲሆን አንድ የቤት መኪና፣የሞባይልና ሞተር ሳይክል መግቢያ ትኬት በ100 ብር ሲቆርጡ አማካይነት በሽልማት መልክ እንደሚወጡ ተገልጿል።

“ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በዛሬው እለት የመንግስት አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ የተከፈተው ።

ይህ ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017 ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን ከታምኮን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩኘ ጋር በመሆን እንዳዘጋጁት ታውቋል።

ኤክስፖው እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ሰምተናል።

መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...