በቤንሻንጉል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

Date:

3 ቀን በሀዘን ታስቦ እንዲውል ተወሰነ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በግልግል በለስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

ዛሬ ግንቦት 10/2017ዓ/ም በግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ከጥዋቱ 3:15 ላይ አንድ ሎቤድ ከላይ ኤክስካባቴር መኪና የጫነ በቴክንክ ብልሽት መስመር ስቶ ሁለገብ ሆቴል ላይ ሻይ ቡና በመጠቀም ላይ ያሉትንና በመንገድ ዳር በግል ስራ ላይ ከነበሩት ሰዎች ላይ በመውጣት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

ከዚህ ቀደምት ብለን በሰራነው ዜገባ የሟቾች ቁጥር 12 መሆንን ብንገልጽም የወደቀው መኪና ከተነሳ በኃላ የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል።

በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወንድ 17 ሴት 2 ድምር 19 ሲሆን ከባድና ቀላል አካል ጉዳት የደረሰባቸው ወንድ 11 ሴት 2 ድምር 13 ሰዎች ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት 55, 500,000 ብር የምሆን ንብረት ላይ ዉድመት መድረሱን የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ  ኮማንደር ታዬ ጉርሜሳ ገልፀዋል::

በእዚህም ምክንያት የመተከል ዞን አስተዳደር በግልገል በለስ ከተማ በደረሰው ከፍተኛ የመኪና አደጋ ምክንያት ለሶስት ቀናት በሀዘን ታስቦ እንደሚውል አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...