በአሜሪካ 250 ሚሊዮን ንቦችን የያዘ የጭነት መኪና መገልበጡን ተከትሎ ነዋሪዎች ወደ አካባቢው እንዳያመሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡
ከንብ በተጨማሪ 31 ኪሎ ግራም የሚመዝን የንብ ቀፎዎችን ጭኖ የነበረው መኪናው በአሜሪካ ግዛት በካናዳ ድንበር አቅራቢያ ባለ አካባቢ ነው የተገለበጠው፡፡
”ባለን አቅም የቻልነውን ያህል ንቦችን ለማዳን እየሞከርን ነው” ሲል የዋትኮም ካውንቲ የሸሪፍ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
ጽ/ቤቱ አያይዞ ንግስት ንቦችን በመጠቀም የተቀሩትን ለመሰብሰብ እየተሞከረ መሆኑን በመግለፅ፤ በ48 ሰዓታት ውስጥ አብዛኞቹን ለመያዝ መታቀዱን አመላክቷል፡፡
ይህም ሂደት እስኪጠናቀቅ በቦታው ላይ ማንም እንደማይንቀሳቀስ ነው የተገለፀው፡፡
የአካባቢው ፖሊስ ክስተቱን ተከትሎ በትጋት እገዛ እያደረጉ ያሉ የአካባቢው ንብ አንቢዎችን አመስግኗል፡፡
አክሎም ከ2 ዶዘን በላይ ንቦች መሰብስብ ችለናል ማለቱን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡
