Home ዜና በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉ

በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉ

በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋሉ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ከጥቂት ወራት በፊት የደረሱ የመሬት መንቀጥቀጦች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ተገለጸ። በተለይም የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. የደረሰው ኃይለኛ የ6.0 ማግኒቱድ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።

በዚህ አደጋ ምክንያት መንገዶች፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታን እየተጠባበቁ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በአፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች የአካባቢ ባለስልጣናት ባደረጉት ግምገማ መሰረት እስካሁን ድረስ 85 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 55 ሺህ የሚሆኑት በአፋር ክልል እንዲሁም 30 ሺህ የሚሆኑት በኦሮሚያ ክልል እንደሚገኙ መረጃዎች አመላክተዋል።

ወርልድ ቪዥን እንዳስታወቀው በተለይም ህጻናት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል። በአካባቢው ከሚገኙ 42 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 37ቱ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በዚህም ምክንያት 5 ሺህ 330 የሚሆኑ የትምህርት እድሜ ያላቸው ህጻናት ትምህርት ማግኘት አልቻሉም።

በተፈናቃዮች ጣቢያዎች ያለው የንጽህና አጠባበቅ ችግር እና የሰዎች መጨናነቅ ህጻናቱን እንደ ወባ፣ ተቅማጥ እና የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ለመሳሰሉት ከባድ የጤና ችግሮች አጋልጧቸዋል ብሏል።

CapitalNews